Devadex

ፍፃሜ ያላት ሴት (The Destiny Woman)

gumroad   $30.00   by tiruye
3d old

ይህ መጽሐፍ የተጻፈበት ዓላማም እኔና ሴት ክርስቲያን እኅቶቼ፣ ከእነዚህ መጽሐፍ ቅዱሳዊ የእምነት አርበኛ እናቶች እና እኅቶች ሕይወት ውስጥ፣ በመንፈስ ቅዱስ ብርሃን በኩል ለትምህርታችን የሚሆነንን ቁም ነገር ሁሉ መውሰድ ነው። ሔዋን፥ ሣራ፥ ርብቃ፥ ራሔል እና ልያ፥ ዮካብድ፥ ሩት፥ አስቴር፥ ሌሎች ብዙ የአዲስ ኪዳን ቅዱሳት እንስት (ሴቶች) በዘመናቸው ቅደም ተከተል በየክፍሉና በየምዕራፉ የምናገኛቸው ሲሆን፣ የመጽሐፈ ሩት ትንታኔ ግን የመጽሐፉ ዋና ሞዴል ተደርጎ መቅረቡን ላሳውቃችሁ እወዳለሁ። የእግዚአብሔር የምሕረት አሻራ የደመቀበት የእኔ ምስክርነት እና የግል ልምዶቼም ተካትተውበታል። የዚህ መጽሐፍ ዋና ትኩረት ሴት እኅቶቼ ይሁኑ እንጂ፣ በመጽሐፉ ውስጥ የሚገኙት መለኮታዊ መልእክቶች ለወንድሞችም ጭምር እንደ ሆነ ከታላቅ አደራ ጋር መናገር እፈልጋለሁ ይህን መጽሐፍ የሚያነብቡ ሁሉ:-  እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት እውነተኛ መልኳን ያገኛሉ።  ፍጻሜ ያላት ሴት የሚኖራትን ክርስቶሳዊ አቋም ይማራሉ።  ለታላቁ ተልዕኮ ይበረታታሉ።  እግዚአብሔር የሰጣቸውን የሕይወት ዓላማ ያላገኙ ሰዎች መፈለግ ይጀምራሉ። ያገኙ ደግሞ አጽንተው እንዲይዙት እምነትን ይጨምራሉ።  ለመለኮታዊ የቤተሰብ ተቋም መረዳታቸውና ክብራቸው ይጨምራል። ልጆቻቸውንም የሚያሳድጉበትን ጥበብ ይካፈላሉ። በክርስቶስ ኢየሱስ ያመንን አማኞች ፍጻሜያችን የዘላለም ሕይወት መሆኑን አሁን በእምነት ተቀብለናል (ዮሐ. 3፥16-18)።

Get it → tiruye.gumroad.com

Found on Devadex — the discovery index for independent software the big search engines bury. More from gumroad.

Report this listing